Observing many people getting marriage, one day I decided to get a wife and told to a lot of people to find a good girl for me.
Saturday, March 3, 2012
የሕይወት ትርጉም
ሰዎች ስለሕይወት ያላችሁ ትርጉም እንዴት ነው? ተብለን ስንጠየቅ
እንደየማንነታችን የምናስቀምጠው የሕይወት ፍልስፍና ይኖረናል። ምንም እንኳ የሁላችንም አመለካከት ለየቅል ቢሆንም
ቅሉ፣ ማጠቃለያችን አንድ ያደርገንና በኖህ መርከብ እንደነበሩት እንስሶች ያዛምደናል።
እኔም
በተለያዩ የህ/ሰብ ክፍሎች የሕይወት ትርጉም ስትቃኝ ምን እንደምትመስል ለማወቅ ፈልጌ በያጋጣሚው የማገኛቸውን በተለያየ ሙያ
ላይ የተሰማሩ ሰዎችን ላናግር ሞክሬያለሁ፤ እስቲ አብረን እያንዳንዳቸው እንደየግብራቸው የሚሉትን እንስማ።
የአዲስ አበባ ፅዳት አልባነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ዋጋ ያስከፍለናል
አንድ
ጊዜ አንድ ወዳጄ ያጫወተኝ ገጠመኝ ነው፡፡ እዚሁ አዲስ አበባ ከተማ አንዱ የሆነ አካባቢ እየሄደ ሳለ ገና ከጉዳዩ ሳይደርስ ሆዱን ክፉኛ ያመዋል፡፡ በነበረበት አካባቢ አንዳችም የሕዝብ መፀዳጃ ቤት የሚባል ነገር የለም፡፡ በእርግጥ ሆቴሎችና ቡና ቤቶች የነበሩ ቢሆንም እዚያ ገብቶ አንዳች የሚበላም ሆነ የሚጠጣ
ነገር አዞ ፊኛውን የሚያቀልበት ቤሳ ቤስቲን የለውም፡፡ ጉድ ፈላ! በድንገት በጠላት እንደተፈታ ከተማ ሆዱ ተሸበረ፤ የት ሄዶ ይተንፍስ? እምን ውስጥ ገብቶ እፎይ ይበል? ጫካ የለ፣ ጉድባ የለ፣ ሰርጥ የለ፣ ብቻ ወዲህ ቢያይ ግዙፍ የመንግሥት መሥርያ ቤት፣ ወዲያ ቢያይ የግል ድርጅት፣ ወዲህ ቢል ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ፣ ወዲያ ቢያይ በሰዎች የተሞላ ካፌ፤ የሆዱን ጉድ የሚገላገልበት ቦታ ፈጽሞ አልነበረውም፡፡ በመጣበት እግሩ ወደራሱ መኖርያ ተመልሶ ነፍሱን ሊዘራ ቢሞክርም፣ እንደ ደራሽ ወንዝ የሆነበት ታችበሌ ፋታ የሚሰጠው አልሆነም፡፡ “ጉዲ ሰዲ!” ይሏል እዚህ ላይ ነው እንግዲህ፡፡
የበላንን የሚያክልን ማነው?
‹‹እንደራሴዎቻችን›› እንደራሳቸው ወይስ እንደራሳችን?
እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ብዙውን ጊዜ ኢቴቪን የምከፍተው ጠቅላይ ሚኒስትራችን ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ የተባለ ሰሞን ነው፡፡ ለምን ቢሉ የሚናገሯቸው በዋዛ የተዋዙት ቁምነገሮች ይመስጡኛልና ነው፡፡ የእውነት ለመናገር ጠቅላይ ሚንስትራችን አንደበተ ርዕቱ ናቸው፡፡ ቅመም ንግግራቸው የባተሌውን ቀልብ ሳይቀር የሚስብ ነው፡፡ የሰሞኑንም የፓርላማ ንግግራቸውን ለመስማት ከቴሌቪዥኔ ፊት ተሰይሜያለሁ፡፡
Thursday, March 1, 2012
እዳ የሚያሳድደው ትውልድ
1-
በጥንት ጊዜ መሬትና ጥንቸል ጓደኛሞች ነበሩ ይባላል፡፡ አብረውም ዕቁብ ይጠጡ ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ጥንቸል ዕቁብ ደረሳት፣ ዕቁቡንም ከበላች በኋላ ተራዋ ደርሶ ‹‹ክፈይ›› ስትባል ‹‹ወገቤን›› አለች፣ አሉ፡፡ ይኸው እስከዛሬም አሻፈረኝ እንዳለች፣ ከመሬት እንደሸሸች አለች ይላሉ አበው ጣፋጭ ወጋቸውን ሲሰልቁ፡፡
የኛንም ትውልድ በኔ መነጽር ስመለከት እንዲህ አይነት ነገር ይታየኛል፡፡
እውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር ወይስ….?
ከዴሞክራሲ ትሩፋቶች አንዱና ዋነኛው ሐሳብን በነፃነት መግለጽ ነው፡፡ እገሌ ይቀየማል፣ እንቶኔ ይሰማዋል ሳይሉ የሆድን የመናገር እውነት፡፡ ዴሞክራሲ ባልዳበረበትና በሌለበት አገር ግን ሐሳብን በነፃነት መግለጽ የሚቻለው ሆድ ሲያባ ብቻ ነው፤ ብቅል ስለሚያወጣው፡፡ በአገራችንም ለበርካታ ዘመናት የእኛ ሰው ‹‹ዕብድና ዘመናይ የልቡን ይናገራል›› በማለት በሥርዓቱ ላይ ያለውን ቅሬታ የሚገልጸው አንድ ሁለት በመጎንጨት ሚስቱ ላይ ነው፡፡ ‹‹አህያውን ፈርቶ ዳውላውን›› እንዲሉ፡፡ አንዳንዱ ደግሞ በተለይ በጣም የተማረና የተመራመረ በሥርዓቱ ላይ ሆዱ ሲጎሽ አውቆ አበድ ይሆናል ወይም ‹‹ሙር›› ይሉታል በያኔው አጠራር፡፡ ከዚያም ያሻውን ቢናገር እሱ ሙር ስለሆነ ወዲያ ተውት ይባላል፡፡ ለአብነት የፍቅር እስከ መቃብሩ ጉዱ ካሣን ልብ ይሏል፡፡
የሙዚቀኞች ፍልሰትና የቤተክርስቲያን ፍዘት
ሰሞኑን አንድ ጽሁፍ እያነበብኩ ሳለ ለብዙ ጊዜ በመንፈሳዊ ሙዚቀኞቻችን ላይ አንዳች እል ዘንድ የሚጎተጉተኝ ሀሳብ ተቀሰቀሰና ብዕሬን ከሰገባው መዝዤ ከብራናዬ ወደርኩ፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)