Tuesday, March 13, 2012

ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ አረፉ የሚል ጭምጭምታ ይሰማል፡፡




ክቡር ፕሬዝደንቱ ዛሬ ማረፋቸውን ጭምጭምታ ወሬ ሰማሁ፡፡ በቅርቡ በጠና ህመም ሆስፒታል መግባታቸውንም ሰምቼ ነበር፡፡ ወሬው የእውነት ከሆነ በጣም ማዘኔን እገልጻለሁ፡፡ ጥሩ ሰው ነበሩና!

ትርጉም፣ የፍልስፍና መጻሕፍትና ተግዳሮታቸው



ዓላማው ሰዎች መጻሕፍትን ያነቡ ዘንድ ማነሣሣት ነው፤ በየአስራ አምስት ቀናት አንድ ጊዜም በተጋበዙ እንግዶችና አባላቱ መካከል በልዩ ልዩ መጻሕፍትና ንባብ ነክ ርእሶች ዙርያ ውይይት የሚያደርገው ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ የመጽሐፍ ንባብና ውይይት ክበብ ነው፡፡ በዕለተ እሕድ የካቲት 25 ቀን፣ 2004 ዓ.ም. በአምስት ኪሎ ብሔራዊ ሙዚየም አዳራሽም ከውጪ አገር በሚተረጎሙ የፍልስፍና መጻሕፍት ዙርያ ሰፋ ያለ ውይይት አድርጓል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬይሽንስ መምህር የሆኑት  አቶ ተሻገር ሽፈራው  በተነሣው ርእስ ላይ ትንታኔና ገለጻ ሰጥተዋል፡፡ ቤቱም አጽንኦት ሰጥቶ ተወያይቶበታል፡፡ ዝግጅቱ ከመጀመሩ በፊትም በቅርቡ በሞት ያጣናቸውን አንጋፋና ስመጥር የጥበብ ሰዎች፣ ደራሲና ጋዜጠኞቹ ስብሐት ገ/እግዚአብሔርና ማሞ ውድነህ በሕሊና ጸሎት ታስበዋል፡፡

በየጊዜው ገበያውን በተቀላቀሉትና እንደ አሸን እየፈሉ በመጡት የውጪ አገር የፍልስፍና መጻሕፍት (በአብዛኛው ሰው አጠራር የሥነ ልቡና መጻሕፍት) የትርጉም ሥራዎች በአንባቢያኑ ዘንድ ስለሚያደርሱት አሉታዊ ተጽዕኖ ውይይት ከመደረጉ በፊት፣ አቶ ተሻገር ገለጻቸውን የጀመሩት መጽሐፍ ማንበብ ለምን ይጠቅማል? በሚል ጥያቄ ነበር ፡፡ ከርሳቸው ገለጻ በኋላም ውይይት ተካሂዷል፤ የነበረውም ድባብ  ደስ የሚል ነበር፡፡ አዳራሹ ካፍ እስከገደፉ ጢም ብሎ በመሙላቱም ምክንያት ብዙ ሰው ውይይቱን የተከታተለው ቆሞና በያገኘበት ተቀምጦ ነበር ፡፡

 አቶ ተሻገር ስለ መጽሐፍ ማንበብ ጥቅምና ስለ አንባቢ አይነቶች ሲናገሩ፡- “ጥሩ መጻሕፍት ማንበብ የአእምሮ ብስለትን ያመጣል፤ የመረዳት አቅምን ያጎለብታል፤ ጠያቂነትን፤ ኃላፊነትንና ምክንያታዊነትን ያጎናጽፋል፡፡ ጆን ስናይደር የተባለው ጸሐፊ አንባቢያንን በሦስት ምድብ ይመድባቸዋል፤ ያየውን ሁሉ ዓሳ ነው ብሎ የሚያጠምድ፣ ወይም ያገኘውን ሁሉ አግበስብሶ የሚያነብ ሰው ከመጀመርያው ምድብ ሲፈረጅ፤ ይህ ሰው በዋናነት መጻሕፍትን የሚያነበው ማንበብ ስላለበት ብቻ ነው፡፡ መራጭ አይደለም፡፡ ሁለተኛው አይነት አንባቢ ደግሞ ስለነገሮች መረጃን ለማግኘት የሚያነበው ሰው ነው፡፡ መራጭ ነው፣ ዓላማው መረጃ አግኝቶ ላቅ ወዳለ ደረጃ መጓዝ ነው፤ የራሱ መመዘኛዎች ስላሉት ምን ማንበብ እንዳለበት ያውቃል፤ ነገር ግን ዋነኛ ዕቅዱ መረጃ ነው፡፡ በሦስተኛው ምድብ ውስጥ የሚገኘው አንባቢ ግን ከሁለቱም ለየት ያለ ነው፡፡ የሥነጽሑፍ አዋቂ ነው፤ ስለተፈጥሮ፣ ስለሰው ልጅና ስለሕይወት በተለየ መልኩ ማወቅ ይፈልጋል፡፡ ዓላማው ማወቅ ነውና፡፡ ምሉዕ ሰብዕና ያለው ሰው ለመሆንም ጽኑ ፍላጎት አለው፡፡”
ከውይይት ተሳታፊዎቹም አንደኛው፡- “አንድ ጸሐፊ መጻሕፍትንና ምግብን ያመሳስላቸዋል፤ ምግብ ሁሉ አንድ እንዳልሆነና የተለያየ ዓይነት ጣዕም እንዳለው ሁሉ መጽሐፍትም እንዲያ ናቸው፡፡ አንድ ጸሐፊ ደግሞ በበኩሉ ሦስት አይነት መጻሕፍት አሉ፤ የሚቀመሱ፣ የሚዋጡ እና የሚሰለቀጡ” ብሎ መጻሕፍትን ከምግብ ጋር አያይዟቸዋል፡፡  ማንበብ ከራስ ታሪክና ባህል ማወቅ ይጀምራል፡፡ የራስን ታሪክ አለማወቅ ትልቅ አደጋ ነውና በማለትም አቶ ተሻገር ከገጠማቸው ተነሥተው ያሉት ነጥብ አለ፡፡

አንዲት በዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምሕርት የምትከታተል የመጨረሻ ዓመት ተማሪ ለመመረቂያዋ  ይረዳት ዘንድ አስባ፣ ስለሕይወቱ  ቃለ መጠይቅ ልታደርግለት ጋዜጠኛ ዘነበ ወላን ትቀጥረዋለች፡፡ በቀጠሯቸውም መሠረት ስትጠይቀው ሲመልስ፣ ስትጠይቀው ሲመልስ፤ ከባሕር ኃይል ተሰናብቶ እንዴት ወደ ጋዜጠኝነቱ ዓለም እንደገባ ትጠይቀዋለች፤ ዘነበም በ1983 ዓ.ም.  በነበረው የፖለቲካ ትኩሳት ምክንያት እንደሆነ ይመልስላታል፡፡ ጀማሪ ጋዜጠኛዋም “በወቅቱ ምን ዓይነት የፖለቲካ ትኩሳት ነበረ?” ብላ አስገርማዋለች፡፡ የቅርቡን ብቻ ሳይሆን የቆየውንም ታሪክ ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በንባብ የሚመጣ ነው፣ ጊዜን ከመጻሕፍትጋ በማሳለፍ የሚገኝ ቁምነገር ነው፡፡”

 ነገር ግን ትውልዳችን ምን ያህል ከመጻሕፍትጋ ያሳልፋል? በየቀበሌውና መንደሩስ ምን ያህል ቤተ መጻሕፍት አሉ? በገዛ ራሳችን ሰዎች የተጻፉስ አገር በቀል መጻሕፍት ምን ያህል በቂ ናቸው? ብለን ብንጠይቅ ለመመለስ አዳጋች አይሆንም፡፡ ህጻን ልጅ ሳለሁ ብዙ ወጣቶች ዳጎስ ያለ መጽሐፍ በጉያቸው ሸጉጠው ሲሄዱ እመለከት ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን የማየው ነገር ሌላ ነው፣ ጫት አለፍ ሲልም ሴት፡፡ ወዴት እየተኬደ ነው? ባንድ ወቅት የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት የነበሩ ስፍራዎች ዛሬ ዛሬ ሌላ ነገር የሚካሄድባቸው እየሆኑ ነው፤ ይህ ነገርስ ዕድገታችንን ሊያመላክት ይችላልን? ብዙ ጊዜ ከውጪ አገር በቀጥታ ቃል በቃል ተተርጉመው የሚቀርቡልን የፍልስፍና መጽሐፍት በአብዛኛው ከባህላችን፣ ወጋችንና ሥርዓታችን ጋር የሚጣረሱ በመሆናቸው ለተርጓሚዎቹም ሆነ ለተደራሲው አስቸጋሪ ናቸው፡፡ የአንዱን አገር ማኅበረሰብ ዕውቀት፣ ባህል፣ ወግና ሥርዓት ላንደኛው ማህበረሰብ አቀብሎ ተለማመደውና ኑርበት ማለት የማይቻል ጉዳይ ነውና፡፡ እዚያ እንደ መልካም ነገር የሚታየው እኛጋ ነውር ሊሆን ይችላል፡፡

በዕለቱ በዋነኛነት የተነሣውም ይኸው ጉዳይ ነው፡፡ እንደ አቶ ተሻገርና የውይይቱ ተሳታፊያን ከሆነም፣ ብዙ የፍልስፍና ትርጉም ስራዎች ትውልዱን እያሳደጉት ሳይሆን ማንነቱን እያሳጡት ነው፡፡ የነኦሾና ዶክተር ራምፓ አይነት መጻሕፍት ምናልባት በተጻፉባቸው ኅብረተረሰብ ባህልና ወግ እሰየው አበጃችሁ ሊባሉ ይችሉ ይሆናል፤ እንደኛ ዓይነት ከብዙ ብሔርና ብሔረሰብ ለተውጣጣና በሃይማኖት ተኮትኩቶ ላደገ ማኅበረሰብ ግን ፋይዳቸው ያን ያህል አይሆንም፡፡” ነበር ያሉት፡፡

አቶ ተሻገር እንደ ምሳሌ ከተጠቀሙዋቸው ግብዓቶችም ሁለቱን ላካፍላችሁ፡፡ ባንድ የአገራችን ብሔረሰብ ሁለት የወንድ ባልንጀሮች ፍቅራቸው ወሰን ልክ አጥቶ ጥግ ሲደርስ፣  ፍቅረኞቻቸውን በጋራ ይተኟቸዋል ይባላል፡፡ እንግዲህ እዚያ ማሕበረሰብ ላይ ተራ የለት ተለት የሆነው ጉዳይ ወደሌላኛው ቢወሰድ ሌላ የባህል ወረራ አሊያም መጥፎ መስተጋብር ሊያስከትል ይችላል ማለት ነው፡፡
አንድ ጊዜ ደግሞ አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በአንድ ክልል ላይ ጥሬ ሥጋ መብላት እንዴት ለበሽታ እንደሚያጋልጥ በፊልም የተደገፈ ትምህርት ይሰጥ ነበር አሉ፡፡  ፊልሙ ካለቀም በኋላ የአካባቢው ማኅበረሰብ አባል ስለፊልሙ ጭብጥ ምንነት ሲጠየቁ የሰጡት ምላሽ “በሁዳዴ ምድር ሥጋ መብላት ለበሽታ ይዳርጋል፤”ነበር፡፡ ወቅቱ የሁዳዴ ጦም ነበርና፡፡

ከውይይት ተሳታፊዎቹም አንዳንዶቹ “ዩኒቨርሲቲዎቻችን በራሳቸው ከተማሪዎቻቸው አቅም በላይ የሆነ የፍልስፍና ትምህርት በመስጠታቸው ብዙ ተማሪዎች አቅላቸውን ይስታሉ፡፡” ብለዋል፡፡  በዘልማድ “ጀዝባ” እየተባሉ የሚጠሩ ብዙ ተማሪዎችም የዚህ ውጤት ናቸው ሲሉ አክለዋል፡፡  አንድ “ጀዝባ” ተማሪ የዩኒቨርሲቲ ትምሕርቱን ለመጨረስ ከሰባት እስከ አስር አመት ሊወስድበትም ይችላል፡፡ ተሳታፊዎቹም ከገጠማቸው ሲናገሩ፡- ካምፓስ እያለን አንድ ጓደኛችን የዶ/ር ራምፓን መጽሐፍ ያነብ ነበር፤ መጽሐፉ ብዙ ማድረግ የማይቻሉ ነገሮችን ሰዎች ይሞክሯቸው ዘንድ የልብ ልብ የሚሰጥ ነው ይባልለታል፡፡ ለምሳሌ፡- “አንተኮ ብረት ነህ፣ እሳት ያግልህ ይሆን ይሆናል እንጂ አያቃጥልህም፡፡” ይላል፤ ታዲያ አንዱ ተማሪ እሳቱን በራሱ ላይ ሞክሮ ያካል ጉዳተኛ ሆኗል፡፡ አንደኛውንም ተማሪ ቀጣይ ኑሮውን በኮርኒስ ውስጥ እንዲያደርግ ገፋፍቶት ላንድ ቀን የዶርሙ ኮርኒስ ውስጥ ካደረ በኋላ በስንት መከራ በእኛ ዕርዳታ ሊወርድ ችሏል ነበር ያሉት፡፡ የቀድሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪው አክለውም መጻሕፍት የሰውን ሰብዕና የመቀየር ኃይል አላቸው፡፡ ተርጓሚዎች ለመተርጎም ሲነሱ ግባቸው ገንዘብ ብቻ መሆን የለበትም፡፡ ብዙ ጊዜ ታዲያ አንዳንድ ትርጉም የፍልስፍና መጻሕፍትን ስናይ ገበያ ተኮር ተደርገው ከመዘጋጀታቸው የተነሳ ርእሳቸው ይጮሃል፤ ውስጣቸው ግን ባዶ ነው፡፡ በትውልዱ ላይም ይህ ነው የማይባል የማንነት ቀውስ እያሳደሩና የባህል ወረራ እያስከተሉ ይገኛሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ግራ የሚያጋቡ የሌላ አገር ባህልና ተሞክሮ ናቸውና በሕይወትና ሰብዕና ላይ የሚያመጡት ተግዳሮት በቀላሉ አይታይም፡፡

 እነዚህ መጻሕፍት እንዴት ባጭር ጊዜ ሀብታም መሆን እንደሚቻል፣ ደግሞም ከስኬት ማማ ላይ እንደሚደረስ ይጠቁማሉ፡፡ ያብዛኛዎቹ ዓላማ ጥረህ ግረህ ብላን ሳይሆን ባቋራጭ ክበር አይነት ነገር ነው ፡፡ ስለሃይማኖትና ባህል፣ ልማድና ወግ፣ ብሎም ፍቅርና ወሲብ አስመልክቶም ከባህላችንና ወጋችን ያፈነገጠ ዕይታ ነው ያላቸው፡፡

ውይይቱ ቀጥሏል፤ አቶ ተሻገርም ለመሆኑ ፍልስፍና ምን ማለት ነው? ሲሉ ለብዙዎቻችን ሩቅና ጠሊቅ የሚመስለውን ጽንሰ ሐሳብ ባጭሩ እንደሚከተለው አስቀምጠውታል፤ ፍልስፍና ከሕይወታችን ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ፍልስፍና በማኅበረሰባችን ውስጥ ያለውን ችግር ወደ ውስጥ ዘልቆ በማየት መፍትሔ ማምጣት ነው፡፡  ለምሳሌ ሕይወት ምንድናት ተብሎ ይጠየቅና ሕይወት እንዲህና እንዲያ ናት እያሉ ትንታኔና ድምዳሜ መስጠት ሊሆን ይችላል፡፡ ከውይይት ተካፋዮቹ መካከል አንደኛው “ፍልስፍና የማንነት ጥያቄ ነው፤ መፈላሰፍ ሲጀመርም እኔ ማነኝ ካለ በኋላ መላ ዕድምተኛውን ፈገግ ያሰኘች ታሪካዊ ገጠመኝ አካፍሏል፤ እንዲህ ነው ገጠመኙ፡፡

 በደርግ ጊዜ ነው አሉ አንድ የወሎ ገበሬ መፈክር አሰማ ተብሎ
“አሜሪካ ትውደም!” ሲል ሠልፈኛው “ትውደም!” ይላል፤
“እንግሊዝ ትውደም!”  ሲል ሠልፈኛው “ትውደም!” ይላል፤
“ሩሲያ ትውደም!” ሲል ግን ሠልፈኛው አጉረመረመ፡፡
“ሩሲያ ትውደም!” ይባስ ብሎ ሠልፈኛው ፀጥ አለ፡፡
“ምንሁናችኋል ጎበዝ ሩሲያ ትውደም! ነውኮ ያልኩት!” ቢል አንድ አዛውንት ድምጻቸውን እየሞረዱ፡-
“ምን ነካህ አያ ሩሲያኮ ዘመዳችን ናት እንዴት ትውደም እንላታለን?” ብለው ቢሉ አስፈካሪው (መፈክር አሰሚው?)፡-
“በምን ሒሳብ ነው ሩሲያ ምትዛመደን ቆቦ ነው ወይስ አላማጣ የተወለደችው?” አለ ይባላል፡፡

አቶ ተሻገር ስለ ፍልስፍና ያንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ አይነት ነገር ሲናገሩም፡- “ፍልስፍና በ Capital ‘‘P’’ (Philosophy) እና በ Small ‘‘p’’ (philosophy) ሲጻፍ የተለያየ ትርጉም አለው፡፡ በ Capital ‘‘P’’ ሲጻፍ እንደ አንድ የዕውቀር ዘርፍ ሲሆን በ Small ‘‘p’’ ሲጻፍ ግን የለት ተለት ሕይወት ይሆናል፡፡ የፍልስፍና አስተሳሰብ ከሕይወትና ኑሮ ጋር የተያያዘ ነው ብለናል፡፡ ደግሞም የ Small ‘‘p’’ ዋን ፍልስፍና (philosophy) ስንጠቀም የለት ተለት ሕይወታችን ይሆናል ስንል አክለናል፤ ለዚህም ለአብነት ያህል ይሆነን ዘንድ ሻላና ዝዋይ አካባቢ የሚኖሩ ያገር ሽማግሌዎችን ፍልስፍና  እንጠቅሳለን” በማለት የሚከተለውን ምሳሌ አጫውተውናል፡፡

አንደኛው አዛውንት ሌላኛውን አዛውንት፡-
“የመሬት መሐሉ የቱጋ ነው?” ብለው ይጠይቃሉ፣
መላሹም “እዚህ እኔ የቆምኩበትጋ ነው ከፈለግህ ከግራና ቀኝ ለክተህ ማረጋገጥ ትችላለህ፡፡” ይላሉ፡፡ እንዴት አይነት አስገራሚ ነገር ነው?. . . የመሬት መሐል እኔ የቆምኩበትጋ ነው፣ ከፈለግህ ዙሪያ ገባዬን ለክተህ አረጋግጥ፡፡ ድንቅ አይደለም? . . . ጠያቂው አዛውንት ይቀጥላሉ፤ “የፈረስህ ፀጉር ብዛት ምን ያህል ነው?” መላሹም፡- “የአንድ ጆንያ ጤፍን ያህል ነው፡፡ ከፈለግህ ለክተህ አረጋግጥ፡፡” ይላሉ፡፡ እንዲህ አይነቱ ፍልስፍና የማረጋገጥን ዕዳ ወደሌላው የማስተላለፍ ሒደት ነው ይባልለታል፡፡ አለቃ ገብረሐና ፈላስፋ ነበሩ፤ ነገር ግን የተሸነፉት ባንዲት ልጃገረድ ፍልስፍና ነው፡፡ እንዲህ ነው የሆነው፤  አለቃ በእንግድነት የዚያች ልጃገረድ ቤተሰብ ዘንድ አርፈው ኖሯል፤ በኋላም ልጃገረዲቱ ለመኝታቸው አጎዛ አንጥፋ “አለቃ ይተኙ!” ብትላቸው አለቃ የአጎዛዋን አናሳነት ተመልክተው፡-“አዬ ልጄ ይበቃኛል ብለሽ ነው?” ብለው ቢጠይቋት ልጃገረዲቱ “ሲጨርሱ ይጨመርልዎታል!” ብላ ቆሌያቸውን ገፋዋለች ይባላል፡፡ እንዲያውም አፈታሪክ እንደሚለው አለቃ ገብረሐና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው መፈላሰፋቸውንና መቀለዳቸውን ያቆሙት፡፡
© ይህ ጽሁፍ በመጠኑ ተሻሽሎ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በእሁድ እትም መጋቢት 2፣ 2004 ዓ.ም. የወጣ ነው፡፡


Saturday, March 10, 2012

እንደ ባዳ... ሲያልፍም እንደ ጠላት

ሰምታችኋል ቻይኖቹ ያሉትንያንን የቀለበትመንገዱን በሚሠሩበት ሰሞን ቀን ያጠሩት የብረት አጥር ሌሊት ተቆርጦ ሲዘረፍ፣ እንዲህ አሉ አሉ፣ “ቆይ ለመሆኑ እናንተ ኢትዮጵያውያን ሌላ አገር አላችሁ እንዴ?” 

ዝም ባለ አፍ ዝምብ አይገባበትም፡፡


በአንድ ማለዳ ወዳጄ ከቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ወደ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ ላይ ፒያሳ የሚሄድ ታክሲ ከሌሎች ተሳፋሪዎች ጋር ችሎት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በርከት ብለው ይጠብቃሉ፡፡ ሰዓቱ እየረፈደ ነው፡፡ ሁሉም ተሳፋሪ ቶሎ ታክሲ አግኝቶ ወደ ሥራ ይሄድ ዘንድ ጓጉቷል፡፡ ነገር ግን ታክሲዎች በሙሉ ከመነሻው ማለትም ከቀጨኔ መድኃኔዓለም እየሞሉ ስለሚመጡ ችግራቸው የከፋ ሆነ፡፡ በዚህን  ጊዜ አንድ ከፒያሳ የመጣ ታክሲ በአጋጣሚ ከመጨረሻው ሳይደርስ መንገድ ላይ ተሳፋሪዎቹን በሙሉ አውርዶ ባዶ ስለነበረ፣ ችሎት አደባባዩ ላይ ያዞርና ወደፒያሳ ለመሄድ ተኮልኩለው የነበሩትን መንገደኞች ማሳፈር ይጀምራል፡፡ በአካባቢው የነበሩ ሁለት የፀጥታ አስከባሪዎች ግን ታክሲው እንዳይጭን ያዙታል፡፡ ‹‹እንዴ ምን ችግር አለው?›› አለ ረዳት፤ ‹‹አደባባይ ላይ ተሳፋሪዎች ወርደው ታክሲው ባዶ ከሆነ እዚህ ብንጭን ምን ችግር አለው?›› አለ ሾፌር፤ ‹‹ምንድነው ችግሩ?›› አሉ ተሳፋሪዎች፤ ‹‹አይቻልም! አዙረህ ሄደህ ከመነሻው ጫን!›› አሉ የፀጥታ አስከባሪዎቹ፡፡

የአፍሪቃ መሪዎች ዋነኛው ችግር

አበው መጨረሻዬን አሳምርልኝ የሚሏት ነገር አለቻቸው፡፡ መጀመርያው አምሮ መጨረሻው ሲበላሽ እንደማየት የሚያስፈራ ነገር የለምና፡፡ የአያሌ አፍሪካ መሪዎች ዋናው ችግር ሌብነት፣ ስግብግብነት፣ ራስ ወዳድነት፣ ብሔራዊ ስሜት አልባነት፣ ቸልተኝነትና ንቀት ብቻ ሳይሆን መጨረሻን አለመገመትም ነው፡፡


 የተራበ እባብ በቀጭኑ የጠርሙስ አንገት አስግጎ ወተት ወዳለበት የጠርሙስ ሆድ ሲገባ በጣም ይቀለዋል ይባላል፡፡ ሲወጣ ግን ጭንቅ ነው፤ ወተቱን ጠጥቶ ሆዱ ተወጥሯልና፡፡ ምናልባት ያለ ችግር ለመውጣት የጠጣውን ሁሉ መትፋት ይኖርበት ይሆናል፡፡


 ብዙዎቹ የአፍሪካ መሪዎች ከሥልጣን የተገረሰሱትም ሆነ ከሥልጣን ኮርቻ ላይ ያሉት የሕዝባቸው ዕዳ አለባቸው፡፡ የመልካም አስተዳደር ዕዳ፣ የዲሞክራሲ ዕዳ፣ ሀሳቡን በነጻነት ይገልጽ ዘንድ አጨብጭቦ መንበር ላይ ለሰቀላቸው ሰው ዕድል ያለመስጠት ዕዳ፣ ያልተዛባ ፍትህ ዕዳና ወዘተ . . . ለዚህም ነው የብዙዎቹ መጨረሻ እንደ ጅማሬያቸው የማያምረው፡፡ አብዛኞቹ የወተቱ ጠርሙስ ውስጥ እስኪገቡ ድረስ ነው ለሕዝብ የቆሙ የሚመስሉት፡፡

Friday, March 9, 2012

ማን ከማን ያንሳል!



የሆነ ጊዜ ሰዎች ሁሉ ጎጆ ሲቀልሱ፣ የሞቀ፣ የደረጀና የደመቀ ኑሮም ሲኖሩ አየሁና እኔስ «ሁ ማይነስ ሁ?» በማለት፣ ከቅን ልቦና በመነጨ ስሜት፣ ገና የትዳርን ሀሁ ሳላጠና፣ እንደ ብልጦቹ ሀብትና  ንብረት ሳላደራጅ፣ ...የማገኛቸውን ሰዎች ሁሉ ሚስት ይፈልጉልኝ ዘንድ ተማጸንኩ። በኋላም ከታላቅ ወንድሞቼ አንደኛው:-

«የእውነት ሚስት ማግባት ትፈልጋለህ?» ይለኛል
«እንዴታ ምን ጥያቄ አለው?» (ፍርጥም ብዬ)
«እንግዲያውስ አንዲት እህት አለች፣ ትዳር ትፈልጋለች፣ ስልኳን ልስጥህና ደውልላት።»
«ስራ አላት?»
«አዎ አላት።»
«ደሞዟ ምን ያህል ነው?»
«አንድ ሁለት ሺ ምናምን… ለዚያውም ‹‹ኤን ጂ ኦ›› ውስጥ ነው የምትሰራው።»

ሕይወት በሐዋርያው ዮሐንስ ዐይን


ስለህይወት ትርጉም የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ያሉትን ጽሁፍ ያነበበ ሰውም  የሚከተለውን አስገራሚ ደብዳቤ ጻፈልኝ።

ውድ ዳዊት እንደምንአለህ?

 ይህቺን መልእክት የምጽፍልህ ከተለመደው ስፍራ ሆኜ እንዳይመስልህ። ማለቴ ምድር ላይ ከሚኖሩት መካከል አይደለሁም። በእርግጥ ባንድ ወቅት እንደ አንተና እንደ መሰሎችህ በምድር ላይ ነበርኩ። አሁን ግን ፈጽሞ አይደለሁም። እኔ በሰማዩ ስፍራ የምኖርና ዜግነቴም ሰማያዊ የሆንኩኝ ነኝ። ምድር ላይ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ አስራሁለቱ ደቀመዝሙሮች አንደኛው ነበርኩ። ኢየሱስንም በጣም እወደው ነበር። እሱም ወደ አምላኩና ወደ አምላካችን ካረገ በኋላ ከሐዋርያት ጋር ሕይወት ማለት ምን ማለት እንደሆነ በብርቱ ሰርተናል። ከሁሉም በላይ ደግሞ በጻፍኳቸውና ለምድር ነዋሪዎች ባበረከትኳው ሶስት መጽሐፎች ማለትም የዮሐንስ ወንጌል፣ የዮሐንስ መልዕክትና፣ የዮሐንስ ራዕይ እታወቃለሁ። ሐዋርያውና ወንጌላዊው ዮሐንስ ነኝ።

ስለ ሕይወት የተለያየ ሙያ ያላቸው ሰዎች የሰጡትን ትርጉም አየሁና ቢገርመኝ ነው ይህን የጻፍኩልህ። ወዳጄ ባጭር አነጋገር ሰዎቹ የሚሉትና ትክክለኛው ሕይወት ትርጓሜ ለየቅል ነው። አንተ ጋዜጠኛው ራስህ ስለህይወት ያለህ ትርጉም ይኼ መሆኑ አሳዝኖኛል።

ዳዊት ለመሆኑ የህይወት ትርጉሙ እውን እናንተ እንዳላችሁት ነው እንዴ?... ፈጽሞ አይደለም። ትክክለኛው የህይወት ትርጉምን ለማወቅ ትፈልጋለህ?... እንግዲያውስ ከመደርደሪያህ ላይ አቧራ የጠጣውን መጽሐፍ ቅዱስህን አንሳና አቧራውን አራግፈህ አንብብ። እዚያ ላይ የህይወት ትርጉም እንደ ማለዳ ጮራ ፍንትው ብሎ ይታይሀል።
በል ታዲያ ትክክለኛውን የህይወት ትርጉም እንዳገኘህ ለተሳሳቱት ሁሉ የህይወት ትርጉሙ ይኼ ነው ብለህ ከስህተት ጎዳና መልሳቸው።

ወደ እኛ ለመምጣት ትጋ። በጽድቅ ጎዳና ተመላለስ። የምስራቹን ወንጌል በጊዜውም ሆነ አለጊዜው ስበክ። እግዚአብሔር ይረዳሀል። ጊዜህ ደርሶም ወደ እኛ እስክትመጣና ሰማያዊ ህይወትህን መምራት እስክትጀምር ድረስ የእግዚአብሔር አብ ፍቅር፣ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና የመንፈስ ቅዱስ እውነት ያግኝህ።

ሐዋርያና ወንጌላዊ ዮሐንስ
ከአዲስቷ ጽዮን

አስገራሚውን  ደብዳቤ አንብቤ እንደ ጨረስኩ ለዘመናት የመጽሐፍት መደርደሪያዬን ከማጣበብ ውጪ አንዳችም ጥቅም ሰጥቶኝ ወደማያውቀውና አቧራ ወደጠገበው መጽሐፍ ቅዱስ እጄን ሰድጄ መዝዤ በማውጣት የእውነት ማንበብ ጀመርኩ።

እንደ መጀመርያም ለምን የዚህን ሐዋርያ ሶስት መጽሐፎች አላነብለትም አልኩና ከዮሐንስ ወንጌል ጀመርኩ። በመጽሐፉ የመጀመርያ ምዕራፍም እንዲህ የሚል ቃል ሰፍሯል።

«በመጀመርያው ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ይህ በመጀመርያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ሁሉ በእርሱ ሆነ፣ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ 
አልሆነም። በእርሱ ሕይወት ነበረች፣ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች ብርሃንም በጨለማ ይበራል፣ ጨለማም አላሸነፈውም።»
 (ዮሐ. ፩፡፩-፭)

በጣም ተገረምኩ። በእርሱ ሕይወት ነበረች፣ ሕይወትም የሰው ብርሀን ነበረች ነው የሚለው። ምን ለማለት ነው? ብዬም ራሴን ስጠይቅ ከጽሁፉ ያገኘሁት መልስ፡-
፩. ሕይወት በእግዚአብሔር ዘንድ መኖሯን
፪. ያም ሕይወት ኢየሱስ መሆኑንና
፫. ሕይወትም ወይም ኢየሱስ የሰው ብርሀን መሆኗን ነው።

(ንባቤን ቀጥያለሁ። ያነሳሁት ነጥብ ስለ ሕይወት ትርጉም ነውና፣ ሕይወትን የተመለከተ ነገር ሳገኝ በማስታወሻ ደብተሬ ላይ አሰፍራለሁ። ደግሞም እንዲህ የሚል ቃል አገኘሁ።)
«በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት  እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።»
(ዮሐ.፫፡፲፮)

(በጣም የሚገርም ቃል ነው። የዘላለም ሕይወት ነውኮ ሚለው። እንዴት ያለ ነገር ነው?... በማን ያመነ ነው የዘላለም ሕይወት የሚያገኘው?.... ንባቤን ልቀጥል፣)

«በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት  አለው። በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።»
(ዮሐ. ፫፡፴፮)

(ምን አለ?... በልጁ የሚያምን?... በማ ልጅ?... እንዴ ሐዋርያ ዮሐንስ ምን እያለ ነው?... ለማንኛውም ንባቤን ልቀጥል…)

«… ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፣ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ፣ የህይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር…»
(ዮሐ. ፬፡፲)

(ምናለ?... የሕይወት ውኃ?... ሐዋርያ ዮሐንስ ምን ለማለት እየፈለገ ነው?... እውን እኛ ከምናውቀው የምድር ውኃ ውጪ ሌላ የሕይወት ውኃ የሚባል ነገር አለ?... ይገርማል… እሺ ሐዋርያው በጣም ኃይለኛ «ኢሹ» ነው ያነሳኸው… ·ረ ቀጥልልኝ ትካርህ ጥሞኛል። )

«… እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፣  እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ  ይሆናል እንጂ።»
(ዮሐ. ፬፡፲፬)

(ሐዋርያው ግራ እያጋባኸኝ ነው። ኢየሱስ እንዲህ አለ እያልክ ነው ያለኸው። ታዲያ ይህ የምትለው ነገር እንዴት ሰዎች ሳይረዱት ቀሩ?... ለምንስ በምድር ላይ ብዙ ሐይማኖት ተፈጠረ?... በክርስትና ስር ራሱ እጅግ በርካታ ሐይማኖቶች አሉ፤ ይህ ለምን ሆነ?... ደግሞም የኢየሱስ ዘር የሆኑት አይሁዶች ራሳቸውኮ አልተቀበሉትም፣ … ለማንኛውም እስቲ ማንበቤን ልቀጥል። )

«እናንተም በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው  ነገር ግን ሕይወት እንዲሆንላችሁ ወደ እኔ ልትመጡ አትወዱም።»
(ዮሐ. ፭።፴፱)

(ከዚህ በላይ ግራ መጋባት ምን አለ?... በጃቸው ያለው መጽሀፍ ስለ ኢየሱስ የሚናገሩና የሚመሰክሩ ከሆኑ፣ ሌላ ኢየሱስ መጠበቅ ስለምን አስፈለጋቸው?... አሁንስ ቢሆን እየሆነ ያለው እንዲህ አይደለም እንዴ?... ኢየሱስ ብቻ ነው የሕይወት ቁልፉ ተብሎ ሳለ ብዙ ሰዎች ግን ቁልፉን አጥተውታል። ቁልፉ በጃቸው ሆኖ ሳለ አላስተዋሉትም፣ ወይ ንቀውታልና ሌላ የሕይወት በር ቁልፍ እየፈለጉ ናቸው። ሲገርም… ለማንኛውም ወደ ንባቤ ልመለስ…)

«ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፡- የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ  ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምን ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም።»
(ዮሐ. ፮፡፴፭)

(እውነታው ግን ብዙዎች ይህንን ቃል አላነበቡትም ወይም አልበራላቸውም ስለዚህም ኢየሱስ የሕይወት እንጀራን ቸል ብለውታል፤ ዳሩ ሰው ካልታዘዘ፣ ካላነበበና ካልሰማ እንዴት ቃሉ ይበራለታል?... እኔን ጨምሮ የብዙዎች መጽሐፍ ቅዱስ አቧራ ከመጠጣት አልፎ ሸረሪት አድርቶበታል።)

«ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።»
(ዮሐ. ፮፡፵

(ወይ ግሩም አያችሁልኝ ሌላ ጉድ?... አያችሁ የእግዚአብሔር አብ ፈቃድ ምን እንደሆነ?... የዘላለም ሕይወት እንድናገኝ የአብ ፈቃድ ነው። ያም በልጁ ስናምን ብቻ ነው። ደግሞኮ ሞተን አንቀርም ምክንያቱም በመጨረሻው ቀን እኔ አስነሳዋለሁ ይላልና ኢየሱስ። አሁን ሕይወትና የሕይወት ትርጉም እየገባኝ ነው። ንባቤን ቀጥያለሁ።)

«እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው።  የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ። ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ  ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ስጋዬ ነው።… እውነት እውነት እላችኋለሁ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ።»
(ዮሐ. ፮፡ ፶፩-፶፬)

«ሥጋ ምንም አይጠቅምም እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።…»

«… ከዚህም የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም። ኢየሱስም ደግሞ ለ አስራሁለቱ እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን? አለ። ስምዖን ጴጥሮስ፡- ጌታ ሆይ ወደማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ  እኛስ አንተ ክርሰቶስ የህያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆንህ  አምነናል አውቀናልም ብሎ መለሰለት።»
(ዮሐ.፮፡፷፰)

(ታዲያ እስከዛሬ የሄድኩበት መንገድ ትክክል አይደለም ማለት ነው? … እስከዛሬ ድረስ የዘላለም ሕይወት እንዴት ማግኘት እንዳለብኝ ማንም የነገረኝ አልነበረም። «ኢቭን» ከናትና አባቴ የወረስኩት ሐይማኖት በራሱ ሰንበትንና በዓላትን ከማክበር ውጪ አንዳችም ቁም ነገር አላስተማረኝም። የናትና አባቴ ሐይማኖትማ ትልቅ ቦታ ሚሰጠው ለአዳኙ እናት እንጂ ለልጇ እንዳልሆነ ጸሐይ የሞቀው ሐቅ ነው። … እውነት ለመናገር ይኸው እስካሁን መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ከጀመርኩበት ሰከንድ አንስቶ አንድም ቦታ ላይ ስለ እናቲቱ አማላጅነት የሚናገር ስፍራ አላገኘሁም። ይልቁንስ የወንጌሉ ዘጠና ዘጠኝ ነጥብ ዘጠኝ የሚያትተው ስለ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ታዲያ ምንድነው ምጠብቀው?... እውን የዘላለም ሕይወት ማግኘት አልፈልግምን?... በጣም እፈልጋለሁ። እንግዲያውስ በኢየሱስ ክርስቶስ ልመና?)

1996 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

Saturday, March 3, 2012

ዜማ እስኪታደስ ጆሮ ዳባ ልበስ


እንደ ብዙ ውሆች ድምጽ ያለ፣ ጋራና ሸንተረሩን አቆራርጦ፣ ገመገሙንና ተረተሩን አሳብሮ፣
ወንዛ ወንዙንና ሰርጣ ሰርጡን ተሻግሮ፣ ሰማያትንና ደመናትን ሰነጣጥቆ፤ እንደ ዕጣንና ከርቤ
ጢስ የንጉሡን እልፍኝ የሚያውድ ነው፤ እኛ ላጤዎች ከየአቅጣጫው ሆነን፣ ከጓዳችን
ተደፍተን፣ ሁነኛ ውሀ’ጣጪያችንን፣ አይን ከዳኛችንን ለማግኘት ለአምላካቸን በእንባና ጸሎት
የምንጽፈው ግጥም ነው ‹‹የትዳር ጸሎት››።

ትዳር በደላላ?


ስለጋብቻ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ብዙ ስፍራዎች ላይ ተጽፏል። ትዳር መልካም እንደሆነ፣ ጋብቻ ቅዱስ መኝታውም ንጹህ እንደሆነና የእግዚአብሔርም ክቡር ሀሳብ እንዳለበት ወዘተ…
እግዚአብሔር አስቀድሞ ሰውን ሲፈጥር በመጀመርያ ብቻውን እንዳልነበረ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘፍ. 1፡36 ላይ ይናገራል። ይህ ስፍራ ምን ያህል እግዚአብሔር ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ እንዳልወደደ የሚያሳየን የመጀመርያው ክፍል ነው። ለዚህም ነው "ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው::" የሚለው። በነገራችን ላይ እግዚአብሔር በመጀመርያ አዳምን (ወንድን) ብቻ ነው የፈጠረ የሚመስለን አይደል?.. ግን በማስተዋል ስናነብ "እግዚአብሔርም ሰውን ፈጠረ፣ ወንድና ሴት አድርጎም ፈጠራቸው::" ይላል። (ዘፍ. 1፡27)

searching for a good wife


Observing many people getting marriage, one day I decided to get a wife and told to a lot of people to find a good girl for me. 


የሕይወት ትርጉም


ሰዎች ስለሕይወት ያላችሁ ትርጉም እንዴት ነው? ተብለን ስንጠየቅ እንደየማንነታችን የምናስቀምጠው የሕይወት ፍልስፍና ይኖረናል። ምንም እንኳ  የሁላችንም አመለካከት ለየቅል ቢሆንም ቅሉ፣ ማጠቃለያችን አንድ ያደርገንና በኖህ መርከብ እንደነበሩት እንስሶች ያዛምደናል። 
እኔም በተለያዩ የህ/ሰብ ክፍሎች የሕይወት ትርጉም ስትቃኝ ምን እንደምትመስል ለማወቅ ፈልጌ በያጋጣሚው የማገኛቸውን በተለያየ ሙያ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን ላናግር ሞክሬያለሁ፤ እስቲ አብረን እያንዳንዳቸው እንደየግብራቸው የሚሉትን እንስማ።

የአዲስ አበባ ፅዳት አልባነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ዋጋ ያስከፍለናል

አንድ ጊዜ አንድ ወዳጄ ያጫወተኝ ገጠመኝ ነው፡፡ እዚሁ አዲስ አበባ ከተማ አንዱ የሆነ አካባቢ እየሄደ ሳለ ገና ከጉዳዩ ሳይደርስ ሆዱን ክፉኛ ያመዋል፡፡ በነበረበት አካባቢ አንዳችም የሕዝብ መፀዳጃ ቤት የሚባል ነገር የለም፡፡ በእርግጥ ሆቴሎችና ቡና ቤቶች የነበሩ ቢሆንም እዚያ ገብቶ አንዳች የሚበላም ሆነ የሚጠጣ ነገር አዞ ፊኛውን የሚያቀልበት ቤሳ ቤስቲን የለውም፡፡ ጉድ ፈላ! በድንገት በጠላት እንደተፈታ ከተማ ሆዱ ተሸበረ፤ የት ሄዶ ይተንፍስ? እምን ውስጥ ገብቶ እፎይ ይበል? ጫካ የለ፣ ጉድባ የለ፣ ሰርጥ የለ፣ ብቻ ወዲህ ቢያይ ግዙፍ የመንግሥት መሥርያ ቤት፣ ወዲያ ቢያይ የግል ድርጅት፣ ወዲህ ቢል ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ፣ ወዲያ ቢያይ በሰዎች የተሞላ ካፌ፤ የሆዱን ጉድ የሚገላገልበት ቦታ ፈጽሞ አልነበረውም፡፡ በመጣበት እግሩ ወደራሱ መኖርያ ተመልሶ ነፍሱን ሊዘራ ቢሞክርም፣ እንደ ደራሽ ወንዝ የሆነበት ታችበሌ ፋታ የሚሰጠው አልሆነም፡፡ጉዲ ሰዲ!” ይሏል እዚህ ላይ ነው እንግዲህ፡፡